ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ስለመከላከያ ሰራዊት

ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ

ጳጉሜ 02/2013 (ዋልታ) የአገር መከላከያ ሰራዊታችን የኩራታችን ምንጭ ነው ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለፁ።

ርዕሰ መስተዳድሩ የሽብር ቡድኑን ሕወሓት ለማጥፋትና በዘላቂነትም የአገራቸውን ሉኣላዊነት ለማስከበር ወደ ወታደር ማሰልጠኛ ማዕከል የገቡትን 4 ወንድማማቾች መነሻ አድርገው ባስተላለፉት መልዕክት ነው ይህን ያሉት።

ለአገር የሚደረግ መሰል ጀግንነትንም ታሪክ እንደሚዘክረው ርዕሰ መስተዳድሩ በቲውተር ገፃቸው ጽፈዋል።