አደገኛው የኮቪድ ዴልታ ዝርያ ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘት

የኮቪድ ዴልታ ዝርያ

ጳጉሜ 02/2013 (ዋልታ) አደገኛው የኮቪድ ዴልታ ዝርያ ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር ይፋ አደረገ።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በሰጡት መግለጫ “በኢትዮጵያ ባለፉት ሳምንታት በወረርሽኙ የሚያዙ ሰዎች፣ የሚሞቱና ፅኑ ህሙማን ቁጥር በጣም አሻቅቧል” ብለዋል።

አዲሱ ዝርያ ሁሉንም የዕድሜ ክልል የሚያጠቃ፣ ለከባድ ህመምና ሞት የሚዳርግ በተለይም ባልተከተቡ ሰዎች ላይ የሚበረታ ዝርያ መሆኑን ገልፀዋል።

ክትባት በየጤና ተቋማቱ በመገኘት እንዲወስዱ፣ የኮቪድ ፕሮቶኮልን ከሁሉም ተቋማትና ግለሰቦች እንደሚጠበቅ ማሳሰባቸውን  ኢዜአ ዘግቧል።

በኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት ብቻ 8 ሺህ 300 ሰዎች በወረርሽኙ ሲያዙ እስካሁን በአገሪቱ 313 ሺህ ሰዎች በበሽታው ተይዘዋል። ከ4 ሺህ 700 በላይ ሰዎች ደግሞ በወረርሽኙ ሳቢያ ሕይወታቸው አልፏል።

በኮቪድ ወረርሽኝ የመያዝ ምጣኔውም ከ1 በመቶ ወደ 20 በመቶ አሻቅቧል፤ ባለፈው ሳምንት 118 ሰዎች ሞተዋል።