ለሰራዊቱ ከ19 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ

ጳጉሜ 2/2013 (ዋልታ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለመከላከያ ሰራዊትና ለክልሉ ልዩ ኃይል ከ19 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ተደረገ፡፡

የኅልውና ዘመቻ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው በዛሬው ዕለት ሥራውን ገምግሟል፡፡

የኅልውና ዘመቻ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኢስሃቅ አብዱልቃድር ቀደም ሲል የተሰበሰበውን ጨምሮ ለመከላከያ ሰራዊት እና ለክልሉ ልዩ ኃይል በጥቅሉ ከ34 ሚሊዮን 216 ሺሕ በላይ የገንዘብ ድጋፍ መሰብሰቡን ገልፀዋል።

የሰራዊት ምልመላን በተመለከተ መደበኛ እና ምልስ በድምሩ 1 ሺሕ 609 እንዲመዘገቡ መደረጉን ኮሚቴው ገልጿል።

በክልሉ 530 የልዩ ኃይል ምልምሎች ወደ ስልጠና እንዲገቡ መደረጋቸውን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።