ጳጉሜ 3 “መልካምነት ለሀገሬ፣ ለወገኔ” ቀን

ጳጉሜ 03/2013 (ዋልታ) የመልካምነት ቀን የሚል ስያሜ የተሰጠው ዿጉሜ 3 “መልካምነት ለሀገሬ፣ ለወገኔ” በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ ይገኛል::

በዚህ መሰረትም በጉለሌ ክፍለ ከተማ እድሳት የተደረገላቸው ቤቶች ለነዋሪዎች ተበርክተዋል::

በመልካምነት ቀን ተሳታፊ የነበሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልካምነት የኢትዮጵያውያን መገለጫ በመሆኑ የበጎነት ስራን ከእለት ተእለት እንቅስቃሴያችን እኩል ልንተገብረው ይገባል ብለዋል::

በዓልን በማስመልከትም 6 ሺህ 500 ለሚሆኑ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ስጦታ ተበርክቷል::

እንዲሁም በዓልን ታሳቢ በማድረግ ሀገርን ለመታደግ ለዘመተው የመከላከያ ሰራዊት ስጦታ ተበርክቷል ተብሏል::

መልካምነት ያለው ለሌለው ማካፈል መርዳት የሚችል እርዳታ ከሚሻው ጎን መቆም ዋነኛ መገለጫዎቹ ናቸው::

በሄብሮን ዋልታው