የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እና ሥርጭት

የሰላም ሚኒስትር ሙፌሪሃት ካሚል

ጳጉሜ 04/2013 (ዋልታ) የሰላም ሚኒስትር ሙፌሪሃት ካሚል ከአለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ፀሃፊ ልዩ መልእክተኛ ራሚሮ ሎፔዝ ዳ ሲልቫ ጋር በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በመንግስት እና የሰብዓዊ አጋሮች እየተከናወነ ባለው የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እና ሥርጭት ዙሪያ ተወያዩ።

ሚኒስትሯ በአማራ እና አፋር ክልሎች የተጀመረውን የሰብዓዊ እርዳታ የማዳረስ ጥረት የማስፋት እና የማፋጠን አስፈላጊናትና ክንውኖች ላይ መወያየታቸውንም በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

ልዩ መልዕክተኛው በውይይታቸው ወቅት የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቱን እንቅስቃሴ ለማፋጠን በቅርቡ በተወሰዱ የማሻሻያ እርምጃዎች መደሰታቸውን እና የተሻለ አፈጻጸም እንዳለ መግለፃቸውን ጠቁመዋል።

ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በመለየት የመፍትሄ ሃሳቦች ላይ መነጋገራቸውንም ሚኒስትሯ አመልክተዋል።