ለ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሐረሪ ክልል ዝግጅት

ጳጉሜ 4/2013 (ዋልታ) ስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ በሐረሪ ክልል ሰላማዊ፣ ነፃና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ በሚቻልበት ዙሪያ በክልሉ ከሚገኙ የፀጥታ አካላት ጋር የተወያዩ ሲሆን፣ በክልሉ ምርጫው ሰላማዊና ነጻ ሆኖ ከፍጻሜ እንዲደርስ ክልሉ ከፌደራል የፀጥታ ኃይሎች ጋር በቅንጅት እየሰራ ነው ብለዋል።

የክልሉ ህዝብ እና ከክልሉ ውጪ የሚኖሩ የሐረሪ ብሄረሰብ አባላት ምርጫው ከፍተኛ ዋጋ እንዳለው በመገንዘብ በንቃት እንዲሳተፉ መልዕክት ማስተላለፋቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።