ሰብኣዊ እርዳታና የአሸባሪው ሕወሓት የረሃብ ፕሮፖጋንዳ

ጳጉሜ 4/2013 (ዋልታ) አሸባሪው የሕወሓት ቡድን ረሃብን እንደጦርነት መሳሪያና ሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳ ማሳለጫ አድርጎ መቀጠሉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ቡድኑ በአንድ በኩል ሰብኣዊ እርዳታን እየዘረፈና በትግራይ ቴሌቪዥን የክልሉ ነዋሪዎች ለታጣቂ ቡድኑ ስንቅ እያዘጋጁ መሆኑን እያሳወቀ በረሃብ ምክንያት ሰዎች እየሞቱ ነው የሚል ፕሮፖጋንዳን እኩል ለማስኬድ መሞከሩ እርስ በእርሱ የሚጣረስ ነው ተብሏል፡፡

ሆኖም መንግሥት በትግራይም ሆነ በአማራና አፋር ክልል በአሸባሪው ሕወሓት ምክንያት ለተፈናቀሉና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ሰብኣዊ እርዳታ እየደረሰ መሆኑን  የጽሕፈት ቤቱ ፕሬስ ሴክሬታሪ ቢሌኒ ስዩም አስታውቀዋል፡፡

ኃላፊዋ እየሰጡት በሚገኘው ሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ፤ ወደ ትግራይ ክልል ሰብኣዊ እርዳታ ጭነው የገቡ ከባድ ተሽከርካሪዎች ቁጥር 535 መድረሱን አሳውቀው ተጨማሪ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደዚያው እያቀኑ ነው ብለዋል፡፡

ከተለያዩ የሰሜን ወሎ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደሴ ተጠልለው ለሚገኙ ወገኖች 150 ሺሕ ወገኖችም ድጋፍ እየቀረበ መሆኑን አክለዋል፡፡

በተጨማሪም በተለያዩ የአማራ አካባዎች በተለይም በዋግምራ ዞን ሰቆጣ ወረዳ እና በጎንደር ፈጥኖ ደራሽ ሰብኣዊ እርዳታ የማድረስ ሥራ እየተከወነ መሆኑን አንስተዋል፡፡