የአሸንዳ በዓል አከባበር በወዳጅነት ፓርክ

የአሸንዳ በዓል አከባበር በወዳጅነት ፓርክ

ጳጉሜ 5/2013 (ዋልታ) አሸንዳ 2013 በአዲስ አበባ ወዳጅነት ፓርክ በደማቅ ሁነታ እየተከበረ ነው፡፡

በመርኃግብሩ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ጨምሮ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ታድመዋል፡፡

አሸንጃ የአንድነት እና የወንድማማችነት ሕያው ማስረጃ ነውም ተብሏል፡፡

በዓሉ የሚከበረዉ ታሪካዊ እሴቶች እና ልዩነቶች ዉስጥ ያለዉን የማይናወጥ አንድነት ለማሳየት ስለመሆኑ ተገልጿል፡፡

የህዝቦች ትስስር በማንም አሸባሪ ጫና ወይም አስገዳጅነት ሳይሆን ከህዝቦች የጋራ ማንነት እና የጋራ ታሪክ የሚቀዳ ከትናንት ታሪክም እና ከዛሬ እዉነታ ነዉ የሚሉ መልዕክቶች ተላልፈዋል፡፡

መርኃግብሩን የትግራይ ግዜያዊ አስተዳደር እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጋራ አዘጋጅተዉታል፡፡

በሰለሞን በየነ