በአሸባሪው ወረራ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ

መስከረም 4/2014 (ዋልታ) በአማራ ክልል ውስጥ የሚገኙ ባለሃብቶች በአሸባሪው ሕወሓት ወረራ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ አደረጉ፡፡

በሰሜን ወሎ እና ደቡብ ጎንደር ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና ባለሃብቶች የጎበኙ ሲሆን ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ባለሃብቶቹ ለተጎጂ ቤተሰቦች ከ11 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የገንዘብ እና የምግብ ድጋፍ ነው ያደረጉት።

የስንዴ ዱቄት፣ ዘይት እና ከፍተኛ ጉዳት ለደረሰባቸው 56 ቤተሰቦች ደግሞ ለእያንዳንዳቸው 10 ሺሕ ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

ባለሀብቶቹ አሸባሪውን ሕወሓት በግንባር እየተፋለሙ ላሉ የፀጥታ አካላትም የ100 ሰንጋዎችን ድጋፍ አድርገዋል፡፡