በጎንደር በቁጥጥር ስር የዋለ ህገወጥ የክላሸና ብሬን ጥይት

የክላሸና ብሬን ጥይት

መስከረም 5/2014 (ዋልታ) በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 በአንድ ህገወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪ ግለሰብ  መኖሪያ ቤት በተደረገ ፍተሻ  4ሺሕ 978 የክላሸና 2ሺሕ 790 የብሬን ጥይት ትላንት በቁጥጥር ስር ውሏል።

ጥይቶቹን በቁጥጥር ስር ማዋል የተቻለው ብሄራዊ መረጃና ደህንነት ከአማራ ክልል ፖሊስ ጋር በመተባበር መሆኑን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።