የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት በተለያዩ ክልሎች

መስከረም 5/2014 (ዋልታ) “የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” በሚል መሪ ቃል በወጣቶች ሊግ አሰተባባሪነት የተዘጋጀው የወጣቶች ንቅናቄ ፕሮግራም በተለያዩ ክልሎች በይፋ ተጀምሯል።

ንቅናቄው በአፋር ክልል በይፋ የተጀመረ ሲሆን፣ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ  ኢሴ አዳም ኢሴ ዘመቻው የኢትዮጵያን እውነታ ለመላው አለም በተለይም ደግሞ ለምዕራባዊያን መንግስታት ለማሳወቅና ለማስረዳት ዓላማ ያደረገ የዲኘሎማሲ አካል ነው ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ የአሸባሪውን ህወሓት የጥፋት ድርጊት ለአለም ለማሳወቅ በተጀመረው ዘመቻ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በይፋ ተጀምሯል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሃሰን ዘመቻውን ባስጀመሩበት ወቅት ሽብርተኛው ህወሓት ሃገር ለማፍረስ ጦርነት አውጆ ተግባራዊ ለማድረግ እየማሰነ ነው ብለዋል፡፡

የ“ነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” ዘመቻ የኢትዮጵያን እውነተኛ መረጃ በመግለጽ የሽብርተኛውን ህወሓት ሃገር የማፍረስ ሴራ ለሌላው ዓለም ለማሳወቅ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ከብልፅግና ፓርቲ እና ከኢዜአ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡