በሄይቲ የአሜሪካ ልዩ መልእክተኛ ዳንኤል ፎቴ ስራ መልቀቅ

መስከረም 13/2014 (ዋልታ) በሄይቲ የአሜሪካ ልዩ መልእክተኛ ሆኖ እንዲያገለግል በባይደን አስተዳደር የተሾመው አሜሪካዊው ዲፕሎማት ዳንኤል ፎቴ ስራ መልቀቁ ተገለፀ።

አምባሳደር ዳንኤል ፎቴ በሐይቲ ልዩ መልዕክተኛ ሆኖ የተሾመው የዛሬ ሁለት ወር ገደማ እንደነበር ሚያሚ ሄራልድ ገልጿል።

በቅርቡ ፕሬዝዳንቷ የተገደሉባት ሄይቲ በሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ቀውሶች እየታመሰች መሆኗ ይታወቃል።

በተለይ አሜሪካ በዩኤስኤ-ሜክሲኮ ድንበር በሀይቲ ስደተኞች ላይ ግፍ መፈፀሟ ይፋ መሆኑን ተከትሎ የባይደን አስተዳደር በሄይቲ የሚያራምደው  ፖሊሲ እንዲተች አድርጎታል።

አምባሳደር ዳንኤል ከሳምንታት በፊትበአንድ ፓናል ላይ “የልዩ መልዕክተኛውን ሥራ ስቀበል አሜሪካ በሄይቲ ውስጥ ተመሳሳይ ስህተቶችን እንደማትደግም በመተማመን ነበር” ብሏል።

ይህ ባለመሆኑ ይመስላል ዲፕሎማቱ የስራ መልቀቂያ አስገብቶ ስራውን እንዲለቅ ያደረገው።

አሜሪካ እያራመደች ያለው የውጭ ፖሊሲ የተሳሳተ ስምህን ከበርካታ ሀገራት ጋር ቅሬታ ውስጥ ከመግባቷም ባሻገር ተቃውሞዎች እየተሰነዘሩባት ይገኛል።

የቀድሞ የሃይቲ ፕሬዝዳንት ጆቬኔል ሜሴ በአሜሪካ ሴራ መገደላቸው ይነገራል።