የክልል መስተዳድሮች አዲስ መንግስት የሚመሰርቱበት ቀን

መስከረም 14/2014 (ዋልታ) የተለያዩ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች አዲስ መንግስት የሚመሰርቱበት ቀን ይፋ አደረጉ፡፡

የአማራ ክልል፣ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል፣ የሲዳማ ክልል እና የጋምቤላ ክልል  በቀጣይ ሳምንት አዲስ መንግስት ይመሰርታሉ፡፡

የአዲሱ መንግስት ምስረታ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል መስከረም 19፣ በጋምቤላ ክልል፣ በአማራ ክልል እና በሲዳማ ክልል መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚሆን ክልሎቹ አስታውቀዋል፡፡

በተጨማሪም፣ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የአዲሱ መንግስት ምስረታ መስከረም 21 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚሆን አስተዳደሩ ማሳወቁን ኢቢኮ ዘግቧል፡፡