በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ተቃውሞ

መስከረም 18/2014 (ዋልታ) በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የአሜሪካ መንግስት ያወጣውን ትዕዛዝ በመቃወም በኋይት ሃውስ፣ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤትና በሲኤን ኤን ቢሮ ፊት ለፊት በመገኘት የተቃውሞ ትዕይንተ ህዝብ አካሂደዋል፡፡

ሰልፈኞቹ በወቅቱ ካስተላለፋቸው መልዕክቶች መካከል ‘ሕወሓት አሸባሪ ድርጅት ነው’፣ ‘አሜሪካ አሸባሪ ድርጅትን መደገፍ አቁሚ’፣ ‘አሜሪካ ኢትዮጵያ አሸባሪዎችን ለማስወገድ የምታደርገውን ጥረት አግዥ’ እንዲሁም ‘ፕሬዝዳንት ባይደን በተሳሳተ ምክር ላይ ተመስርተው ያሳለፉትን ውሳኔ ያንሱ’ የሚሉት እንደሚገኙባቸው ከዲያስፖራ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ  ያመለክታል፡፡