የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት አቶ ኡሞድ ኡጁሉን ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾመ

መስከረም 20/2014 (ዋልታ) – የጋምቤላ ህዝቦች ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት መስራች ጉባዔ አቶ ኡሞድ ኡጁሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድረጎ መረጠ።

አቶ ኡሞድ ኡጁሉ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

ጉባዔው ወ/ሮ ባንቺአየሁ ዲንገታን ዋና አፈጉባዔ እንዲሁም ወ/ሮ ትሁት ሀዋሪያትን ደግሞ  ምክትል አፈ ጉባዔ አድርጎ መምረጡ ይታወቃል።

ኢብኮ እንደዘገበው መስራች ጉባዔው ክልሉን በቀጣይ የሚያገለግሉ የካቢኔ አባላትና ሌሎች ሹመቶችን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።