ፌስቡክ ለሰዓታት በመቋረጡ የማርክ ዙከርበርግ ሃብት ክስረት ደረሰበት

መስከረም 25/2014 (ዋልታ) በፌስቡክ ለሰዓታት በመቋረጡ ብቻ የማርክ ዙከርበርግ የግል ሃብት በ7 ቢሊየን ዶላር ዝቅ ማለቱን የብሉምበርግ ዘገባ አመላከተ፡፡

ለሰዓታት ተቋርጦ የነበረው ፌስቡክን ጨምሮ የዋትስአፕ፣ ኢንስታግራም እንዲሁም ሜሴንጀር አገልግሎት መመለሱን የፌስቡክ ካምፓኒ አስታወቋል፡፡

ተቋርጦ የነበረዉ የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ከተሳሳተ የአወቃቀር ለውጥ ጋር ተያይዞ   እንደነበርም ተገልጿል፡፡

የማህበራዊ ሚዲያው ተቋርጦ በነበረበት ወቅት የተጠቃሚ ግላዊ መረጃ ተጥሷል የሚል ማስረጃ አለመኖሩን ካምፓኒው ጠቁሟል፡፡

የአገልግሎት መቋረጥን የሚከታተለው ዳውደክተር እስካሁን በዓለም ዙሪያ 10 ነጥብ 6 ሚሊየን የሚሆኑ የችግር ሪፖርቶች እንዳሉ አስታውቋል፡፡

የፌስቡክ መስራች ማርክ ዙከርበርግ በመቋረጡ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎችና ካምፓኒዎች ይቅርታ ጠይቀዋል።