ብሔራዊ ባንክ የብድር ገደብ ላይ ማሻሻያ አደረገ

መስከረም 25/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቅርቡ ከብድር አቅርቦት ጋር በተያያዘ በጣለው እገዳ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

በማሻሻያው ባንኮች አምስት የብድር ዓይነቶችን መፍቀድ እንደሚችሉ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

እነዚህም ባንኮች የሰጡትን ብድር ለማስመለስ ሐራጅ ያወጧቸውን ንብረቶች ለመግዛት ለሚጠይቁ ገዥዎች ስለሚሰጥ ብድር፣ በሁለተኛና በሦስተኛ ወገን መካከል የሚደረግ ግብይትና ለባንክ ሠራተኞች ስለሚሰጥ አስቸኳይ ብድር ነው፡፡

በተጨማሪም ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልተው መኖሪያ ቤት ለመግዛት ወይም ለመገንባት ከታመነባቸው  ጠያቂዎች ስለሚሰጥ ብድር፣ ከፀደቁ ድርጅቶችና ከተቋም ሠራተኞች ለሚቀርቡ የብድር ጥያቄዎች እንዲሁም በጎንደር አካባቢ ለሚገኙ የሰሊጥ አምራች ብድር ጠያቂዎች ላይ ማሻሻያዎች ተደርገዋል፡፡