የደቡብ ኮሪያ ዘመናዊ የንብ ቀፎ መቆጣጠሪያ ድጋፍ

መስከረም 27/2014 (ዋልታ) የደቡብ ኮሪያ መንግስት ዘመናዊ የንብ ቀፎ መቆጣጠሪያ ለግብርና ሚኒስቴር ድጋፍ አደረገ፡፡

ማሽኑ በንቦች ላይ ምንም አደጋ ሳያስከትል የደረሰውን ማር ብቻ ከቀፎው ለማውጣት የሚረዳ ነው ተብሏል፡፡

የማሽኑ ክብደት ቀላል ስለሆነ ከቦታ ቦታ ለማንቀሳቀስ እና ለአጠቃቀም ምቹ በመሆኑ ማንኛውም ንብ አናቢ በቀላሉ መጠቀም እንደሚያስችል ተጠቅሷል፡፡

ለሙከራ የመጡት  ማሽኖች ለሆለታ ምርምር ማዕከል፣ ያዩ እና ሸካ የእናት ንብ ማራቢያና ማሰልጠኛ ማዕከላት ተልኮ በዘርፉ በተሰማሩ ባለሙያዎች በሙከራ ከተረጋገጠ በኋላ በቀጣይ ግለሰቦች፣ ባለሃብቶች እና ማህበራት ገዝተው እንዲጠቀሙ ይደረጋል ነዉ የተባለው፡፡

የድጋፍ ርክክብ ስነሥርዓቱ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) እና የደቡብ ኮሪያ ተወካዮች በተገኙበት መካሄዱን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡