ዶ/ር ስለሺ በቀለን ጨምሮ ለተለያዩ ግለሰቦች ሹመት ተሰጣቸው

መስከረም 27/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ  በዛሬው ዕለት አቶ ተፈሪ ፍቅሬን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አድርገው በድጋሚ የሾሙ ሲሆን፣ ለ4 ከፍተኛ የሃላፊነት መደቦችም በሚኒስትር ማእረግ የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል፡፡

  1. አቶ አደም ፋራህ – በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ
  2. አቶ ተስፋዬ ቤልጅጌ – በሚኒስትር ማዕረግ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ
  3. ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) – በሚኒስትር ማዕረግ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የህዳሴ ግድብ ዋና ተደራዳሪና አማካሪ
  4. ዶ/ር ለገሰ ቱሉ – በሚኒስትር ማዕረግ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ

በተጨማሪም፡

– ዶ/ር ምህረት ደበበ – የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት፤

– አቶ ፍሰሃ ይታገሱ – የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ፤

– እንዲሁም አቶ አብዱራህማን ሩቤ – የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡