አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6ሺሕ 163 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው  

መስከረም 29/2014 (ዋልታ) አዲስ በባ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን 6ሺሕ 163 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት እያስመረቀ ነው።

ዩኒቨርሲቲው በወዳጅነት አደባባይ እያስመረቀ የሚገኘው ምሩቃን በመደበኛ፣ በማታና በርቀት ትምህርት መርኃግብር የሰለጠኑ የቅድመ ምረቃና ድሕረ ምረቃ ተማሪዎች ናቸው።

ከተመራቂዎቹ መካከል 155 የሶስተኛ ዲግሪ ዕጩ ምሩቃን መሆናቸው ተጠቁሟል።

በምርቃ ስነ ስርዓቱ የትምህርት ሚኒስትር ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተገኝተዋል።

ከተመራቂዎቹ መካከል  2 ሺሕ 559 ድሕረ ምረቃ፣ 3 ሺሕ 604 የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ሲሆኑ፤ 1 ሺሕ 883ቱ ሴቶች መሆናቸውም ተመላክቷል።

በዙፋን አምባቸው