ዋልታ በክረምት በጎ ፈቃድ ያደሳቸውን የአቅመ ደካማ ቤቶች አስረከበ

መስከረም 29/2014 (ዋልታ) – ዋልታ ሚዲያ እና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት በኦሮሚያ ክልል ጫንጮ ከተማ በክረምት በጎ ፈቃድ መርኃግብር ያደሳቸውን የአቅመ ደካማ ቤቶች በዛሬው እለት አስረከበ፡፡

ተቋሙ እየተገበረ የሚገኘውን የበጎ አድራጎት ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈፃሚ ንጉሴ መሸሻ (ዶ/ር) ተናግረዋል::

የቤት እድሳት የተደረገላቸው አቅመ ደካሞች ለተደረገላቸው እገዛ አመስግነዋል፡፡