ተማሪዎችን በእውቀት አንፆ ወደ ስራ እንዲሰማሩ ማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦው አለው – ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ

መስከረም መስከረም 29/2014 (ዋልታ) – ኢትዮጵያ በአስቸጋሪ ሁኔታ በምትገኝበት ወቅት ተማሪዎችን በእውቀት አንፆ ወደ ስራ እንዲሰማሩ ማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ፡፡

አዲስ በባ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን 6ሺሕ 163 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት እያስመረቀ ይገኛል፡፡

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት ፕሬዝዳንቷ ተማሪዎችን በተሰማሩበት የሙያ ዘርፍ ሰላምና አንድነትን በማምጣት ለውጥ ፈጣሪ ሊሆኑ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጣሰው ወልደሀና (ፕ/ር) በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ ከገባችበት ፈተና እንድትወጣ ተማሪዎች በተማሩበት የሙያ ዘርፍ የማገልገል ግዴታ እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

አክለውም ኢትዮጵያ በዴሞክራሲ ስርዓት ህዝብ ያስተዳድረኛል ያለውን መንግስት በመሰረተበት ወቅት ተማሪዎቹ መመረቃቸው ስነ ስርዓቱን ልዩ ያደርገዋልም ብለዋል፡፡