ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ከበነፊት ኮርፖሬሽን ፎር አፍሪካ አባላት ጋር ተወያዩ

መስከረም 30/2014 (ዋልታ) ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በአሜሪካ በሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች ከተቋቋመው ከበነፊት ኮርፖሬሽን ፎር አፍሪካ (BCA) አባላት እና ከፌደራል ህብረት ሥራ ኤጀንሲ የሥራ አመራሮች ጋር ፡፡

በዚህ ወቅት BCA ከህብረት ሥራ ማህበራትም ሆነ ከአነስተኛ ገበሬዎች ጋር በመተባበር ምርቶቻቸውን ወደ ውጭ በሚልኩበት መንገድ ላይ የያዘውን ዕቅድና አርሶ አደሮች ለሚያመርቱት ምርት ተገቢውን ዋጋ እንዲያገኙ ስለሚደረገው ጥረት ማብራሪያ መስጠታቸውን ከፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡