በመዲናዋ የ2014 ዓ.ም ትምህርት ተጀመረ

ጥቅምት 01/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ ምዕራፍ የመጀመሪያ ደረዳ ትምህርት ቤት በመገኘት የ2014 ዓም ትምህርት አስጀመሩ።

በትምህርት ቤቱ ከንቲባዋ እንዲሁም ሌሎች አመራሮች ተገኝተው የዘንድሮውን ዓመት ትምህርት አስጀምረዋል።

በዛሬው እለት በአዲስ አበባ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ትምህርት መጀመራቸውን ከከተማው ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡