የሰንደቅ ዓላማ ቀን በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ ተከበረ

የሰንደቅ ዓላማ ቀን

ጥቅምት 01/2014 (ዋልታ) “በአዲስ ምዕራፍ በተሟላ ሉዓላዊነት ለሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ” በሚል መሪ 14ኛው የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አፈጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልቃድር፣ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት ተከብሯል።

ቀኑ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ሁሉም መንግስታዊና መንግታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ በትምህርት ቤቶች፣ በወታደራዊ ካምፖች፣ ኤምባሲዎች እና በሌሎች ተቋማት ሰንደቅ ዓላማ በመስቀል መከበሩን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬተሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።