የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 2ሺሕ 526 ተማሪዎች እያስመረቀ ነው።
በኢትዮጵያ ብቸኛ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሆነው ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ በዲፕሎማ፣ በመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም በሁለተኛ ዲግሪ ያስተማራቸውን 1 ሺሕ 285 ወንድ 1 ሺሕ 241 ሴት በድምሩ 2 ሺሕ 526 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት እያስመረቀ ነው።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ብርሀነመስቀል ጠና (ዶ/ር) የዘንድሮ ተመራቂዎች ሀገር በተለያዩ ችግርች ውስጥ ባለችበት ወቅት መመረቃችሁ በርካታ ኃላፊነት እንድትወስዱ ምክንያት ይሆናችኋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም በሁለንታዊ ብልፅግና ሀገርን ማገልገል እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ የክብር ዶ/ር አባዱላ ገመዳ የምረቃ በዓሉ ለሌላ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግርና ሀገርን ለማገልገል ቁርጠኛ ለመሆን የሚያግዝ ነው ብለዋል።
በዙፋን አምባቸው