በደቡብ ክልል የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ተጀመረ

በደቡብ ክልል የፖሊዮ ክትባት

ጥቅምት 12/2014 (ዋልታ) ከ3 ሚሊየን በላይ ህጻናት የሚከተቡበት የደቡብ ክልል የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ተጀመረ።

በደቡብ ክልል ለቀጣዮቹ 4 ቀናት በዘመቻ መልክ የሚሰጠው የፖሊዮ ክትባት በይፋ ተጀምሯል።

የክልሉ የክትባት ዘመቻ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ አሮሬሳ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ላይ ተጀምሯል።

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ፣ የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ እንደሻው ሽብሩ፣ የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም የፌደራል፣ የክልልና የዞን ተወካዮች ወላጆችና ህጻናት ተገኝተዋል።

በክልሉ በአጠቃላይ እድሜያቸው አምስትና ከዛ በታች የሆኑ ከ3 ሚሊየን በላይ ህጻናት የክትባቱ ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በዚሁ መሰረት ወላጆች፣ ትምህርት ቤቶችና ሌሎችም ተቋማት ህጻናትን እንዲያስከትቡ የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ጥሪ ማቅረቡን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክተል።