የደሴ ከተማ ወጣቶች ወደ ግንባር እየዘመቱ ነው

ጥቅምት 16/2014 (ዋልታ) የደሴ ከተማ ወጣቶች የአሸባሪውን ሕወሓት ወረራ ለመቀልበስና ቡድኑን እስከወዲያኛው ለመደምሰስ ወደ ግንባር እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡
አሸባሪው ቡድን ለዓመታት አብዝቶ በደል ሲያደርስባቸው የቆዩት የደሴ ከተማ ወጣቶች “በድጋሚ የበደልን ቀንበር ልንሸከም የምንችልበት ምክንያት የለም” ብለዋል፡፡
በዚህም በሺሕዎች የሚቆጠሩ የሰለጠኑ እና የተደራጁ ወጣቶች ደሴና ኮምቦልቻን ለማያዝ አሰፍስፎ የመጣውን አሸባሪውን ሕወሓትን ለመደምሰስ እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡
በዘመቻው ከደሴ ከተማ ወጣቶች በተጨማሪ ከሰሜን ወሎና ደቡበ ወሎ ዘን የተውጣጡ ወጣቶች ተካተዋል፡፡ ዘመቻውን የመንግሥትና የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎችም እያስተባበሩት ነው፡፡
ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖና ሚሊሺያ በወሎ ግንባር በወረባቦ፣ ተሁለደሬ፣ ኩታበርና ደላንታ በወሰዱት የፀረ ማጥቃት እርምጃ በጠላት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እያደረሱ ስለመሆኑ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ትናንት አመሻሽ ማሳወቁ ይታወሳል፡፡
ጠላት በእነዚህ አካባቢዎች ያሰለፈው ኃይል ሙትና ቁስለኛ ሲሆን ከጥቃቱ የተረፈውም እግሬ አውጪኝ በማለት እየፈረጠጠ ይገኛልም ነው ያለው።
በሳራ ስዩም (ከደሴ)
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!