የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲና ኢጋድ ተወያዩ

ጥቅምት 17/2014 (ዋልታ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) በጋራ በሚስሩባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ።
የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ይድነቃቸዉ ወርቁ ኤጀንሲዉ ከኢጋድ ጋር የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አንስተዉ በይበልጥ በምርምርና ልማት፣ በአቅም ግንባታ እንዲሁም በሳይበር ደኅንነት ላይ በጋራ እንሰራለን ብለዋል።
የኢጋድ የደኅንነት ዘርፍ ኃላፊ ኮማንደር አበበ ሙሉነህ በበኩላችው ኢጋድ በሰው ኃይል ማብቃት፣ በጥናትና ምርምር እንዲሁም በማማከር ዘርፍ ከኤጀንሲው ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን እንደገለፁ ከኤጀንሲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።