የደባርቅ ከተማ ህዝብ ከክልሉ መንግስት የቀረበለትን ጥሪ ተቀበለ

ጥቅምት 22/2014 (ዋልታ) የደባርቅ ከተማ ህዝብ ወራሪውን እና ተስፋፊውን የአሸባሪው ሕወሓት ቡድን ለመደምሰስ ወደ ግንባር ለመዝመት የቀረበለትን ጥሪ ተቀብሎ ለግዳጅ መዘጋጀቱ ተገለጸ።
የደባርቅ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ብርሀኑ ፀጋዬ “ጠላት በነሃሴ 2013 ዓ.ም በራችን ድረስ መጥቶ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ሙሉ በሙሉ በፀጥታ ኃይላችን እና በወጣቱ ክንድ ተደቁሶ የተረፈው እግሬ አውጭኝ ብሎ መፈርጠጡ ይታወቃል፤ ዛሬም እንደ ትናንቱ ካለበት አቅራቢያ ወረዳ ህዝባችን አነቃንቀን ድል እናደርገዋለን” ሲሉ ተናግረዋል።
የደባርቅ ከተማ ብልፅግና ጽ/ቤት ኃላፊ መብራቱ ሙሉጌታ ጥሪውን ተቀብለው በአፍጣኝ ለተሰባሰቡት የከተማዋ ነዋሪዎች ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን “አደረጃጀታችን አጠናክረን የተቃጣብንን የህልውና ዘመቻ እንመክታለን” ማለታቸውን ኢፕድ ነው የዘገበው፡፡
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!