ለጎንደር ከተማ ዘማቾች ሽኝት ተደረገ

ጥቅምት 23/2014 (ዋልታ) የመንግሥትን ጥሪ የተቀበሉ የጎንደር ከተማ ዘማቾች ሽኝት ተደረገላቸው፡፡

በአሸናኘት ስነ ሥርዓት ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል እንደገለፁት፤ ትሕነግ ሀብታችን ዘርፏል፣ የሃይማኖት ተቋማትን አቃጥሏል፣ ሴቶችን ደፍሯል፡፤ “የምንዋገው ለፍትህና ለነጻነት ነው፡፡
የአማራ ህዝብ የተቃጣበትን ጦርነት በድል እንደሚያጠናቅቀው እተማመናለሁ ሲሉም ገልጸዋል፡፡
የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዘውዱ ማለደ በበኩላቸው የተቃጣብን ወረራ ለመመከት ያጋጠመው የአመራርና የአደረጃጀት ክፍተቶች የተሞሉ መሆኑን ገልጸው በሁሉም ግንባር ዘመቻው በድል ይጠናቀቃል ብለዋል፡፡
ዘማቾችም በዚህ ታሪካዊ ጦርነት በመሳተፋቸው ደስተኛ መሆናቸውን ከጎንደር ከተማ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡