የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲ መግለጫ

ጥቅምት 23/2014 (ዋልታ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት በወቅታዊ ክልላዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል።
የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከለተው ቀርቧል።
በኢትዮጵያ ህዝቦች መራራ ትግል የተገኘው ለውጥ በውስጥ ባንዳዎች አይደናቀፍም!
አሻባሪው የህወሓት ቡድን ባለፉት 27 ዓመታት ኢትዮጵያን በዘር፣ በሃይማኖት፣ በጎሳና በጎጥ ከፋፍሎ ሲመዘብር መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ቡድን እኔ ያልመራኋት ኢትዮጵያ አትኖርም በሚል እሳቤ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ያለ የሌለውን ኃይል አሰባስቦ ዘምቶብናል።
ባለፉት 3 የለውጥ ዓመታት በህዝቦች ከፍተኛ መስዋእትነት የተገኘውን ሀገራዊ ለውጥ ለመቀልበስ በተለያዩ ጊዜያት ሞክሮ ያልተሳካለት ይሄው አሸባሪ ቡድን ጥቅምት 24/2013 ዓ ም በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የሚገኘውን የሰሜን እዝ የሃገር መከላከያ ሰረዊታችን ላይ ጥቃት በመሰንዘር ኢትዮጵያውያን በይፋ መውጋት ከጀመረ ድፍን አንድ ዓመት ሊሞላው ዋዜማው ላይ እንገኛለን።
በሰሜን ዕዝ ጥቃት እጅግ የተቆጣው የሃገር መከላከያ ሰራዊት እና መላው ህዝባዊ የፀጥታ ሃይሎቻችን በተወሰደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ የጥቃቱ ጠንሳሾችና ባለቤቶችን ለሕግ ማቅረብ፣ እርምጃ በመውሰድና የቀሩትን መበተን ቢቻልም፣ በሕግ ማስከበሩ የተጎዱ የትግራይ አከባቢዎችን መልሶ ለማቋቋምና አርሶ አደሮች እርሻቸውን ተረጋግተው እንዲያርሱ የተወሰደውን የአንድ ወገን ተኩስ አቁም አሸባሪ ቡድኑ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በመላው የአፋር እና የአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ወረራውን አስፋፍቷል፡፡
በዚሁ መሰረት ጁንታው የትህነግ ቡድን በፈጸማቸው አረመኔያዊ ጥቃቶች ንጹሐን ተገድለዋል፣ በሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፣ በሰው ልጅ ላይ ለመፈፀም ቀርቶ ለማሰብ የሚከብዱ አስነዋሪ ኢሰብዓዊ ድርጊቶችን በመፈፀም እኩይ ተግባሩን በግልጽ ከማሳየቱም አልፎ ለዘመናት የተገነቡ የህዝብ መሰረተ ልማቶችን በመዝረፍና የቀረውን በማውደም ኢትዮጵያን ለማዋረድና ሀገራችንን ለማፍረስ እኩይ ተግባሩን በስፋት ቀጥሎበታል። በሴቶች እህቶቻችን ላይ አሳዛኝና አስነዋሪ ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች ተፈጽሟል።
ይህ ቡድን ከተቻለ ኢትዮጵያዊያንን በኃይል በማንበርከክ ወደ ቀድሞ ስልጣን ለመመለስ ካልሆነ እሱ ያልመራትን ኢትዮጵያን ለማፍረስ የኢትዮጵያን አንድነትና ጥንካሬ የማይፈልጉ ታሪካዊ የውጪ ጠላቶችና የውስጥ ባንዳዎችን አስተባብሮ የክህደት ተግባሩን አጠናክሮ ቀጥሏል።
በዜጎች አልህ አስጨራሽ መስዋትነት የመጣውን ለውጥ በአልባሌ መንገድ አሸባሪው ህወሓት ጁንታ ቡደን መና ለማስቀረት የሚያደርገው ጥረት በአይበገረው ህዝባችናን ዘንድ ፍጹም ተቀባይነት የለውም፡፡
ስለሆነም በሀገር ሉዓላዊነት ላይ ድርድር የማያውቀውን የኢትዮጵያ ህዝብ በዘር፣ በፖለቲካና በሃይማኖት ሳይለያይ አሸባሪው የህወሓት ጁንታ ቡድን ሀገር ለማፍረስ የያዘው እቅድ በአማራና አፋር ክልል ሕዝብ ላይ እየፈጸመ ያለውን ጥፋት በጋራ ይመክታል።
በተላላኪዎቹ አማካይነት በውክልና ጦርነት በክልላችን ቡደኑ የሚያደርገው መፍጨርጨር በሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ በፀጥታ ኃይላችንና በህዝባችን የተባበረ ክንድ እየተመከተ በመሆኑ ውርደትን እየተከናነበ እንደሆነ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡