ጥቅምት 24 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሻማ በማብራት ታሰበ

ጥቅምት 24 /2014 (ዋልታ) ‹‹አልረሳውም! እኔም የኢትዮጵያ ሰራዊት ነኝ›› በሚል መሪህ ቃል በአሸባሪው ሕወሓት የተሰውትን የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት በማሰብ የህሊና ፀሎት እና የሻማ ማብራት ሥነሥርዓት ተካሂዷል፡፡
በመርኃግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የሰራዊት ግንባታ ስራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ ተገኝተዋል።
የጥቅምት 24 ሰማዕታት ሲታሰቡ ለአገር የተከፈለ ውለታን የምናስብበት የደም መስዋዕት የተከፈለበት አይረሴ ታሪክ መሆኑ ተጠቅሷል።
የፈሪ በትር እንዲሉ ሽብርተኛው ሕወሓት የሰላሙን ዘብ የችግሩ ፈጥኖ ደራሽ የትግራይ ህዝብ ደጀን የሆነውን ሰራዊት በአደባባይ ከዳው።
በዱር በገደሉ እየተዋደቀ የአገርን ሉአላዊነት የሚያስጠብቀው የመከላከያ ሰራዊት በገዛ ወገኑ ተወጋ ታላቅ ክህደትም ተፈፀመበት።
ጥቅምት 24 ሽብርተኛው ሕውሓት በአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈፀመው ክህደት መላው ኢትዮጵያውያንን አንገት ያስደፋ ተግባር መሆኑ ተገልጿል።
በእለቱም ከተለያዩ የሀይማኖት ተቋማት የተውጣጡ የሀይማኖት አባቶች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ዛሬ በመላው ኢትዮጵያ ብሎም በመዲናዋ አዲስ አበባ ሰማዕታቱን በማሰብ ተውሏል።
በሃኒ አበበ