‹‹እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል›› የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ጥቅምት 24 /2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተባበሩት መንግሥታት የሰብኣዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ከኢትዮጵያ የሰብኣዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ያደረጉትን የምርመራ ሪፖርት ውጤት ተከትሎ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በግኝቱም አሸባሪው ሕወሓት ያደራጃቸው ሳምሪ የተባሉ የወጣቶች ህቡዕ ገዳይ ቡድን በማይካድራ ማንነትን መሰረት አድርጎ የፈፀመውን ጭፍጨፋ ሪፖርቱ ያጋለጠ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግሥት አንዳችም ማንነትን መሰረት ያደረጉ እርምጃዎች እንዳልወሰደ ምርመራው በተግባር ያረጋገጠ ነው ብለዋል።
የምርመራ ውጤቱ “አበው እንደሚሉት እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል ነውና ለዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብና ሚዲያዎቻቸው ጭምር ሆን ብለው ጆሮ ዳባ ልበስ ያሉት የንፁሀን ደም በከንቱ ፈሶ እንዳልቀረ” ማሳያ መሆኑንም ነው የጠቆሙት።
አሁንም ለመላው ዓለም የያዝነውን እውነት እስከመጨረሻዋ ሰዓት ድረስ ማስተጋባታችንን እንቀጥላለን ማለታቸውን ከአስተዳደሩ የፕሬስ ሰክሪታሪያት ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!