አሸባሪዎቹን ሕወሓት እና ሼነን የሚያወግዝ ሰልፍ በወላይታ ዞን እየተካሄደ ነው

ጥቅምት 27/2014 (ዋልታ) ለጀግናው አገር መከላከያ ሠራዊት ደጀንነትና አጋርነትን የሚገልጽ ድጋፍ እና አሸባሪዎቹን ሕወሓት እና ሼነን የሚያወግዝ ሰልፍ በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በጀግኖች ኢትዮጵያውያን ተጋድሎ ተጠብቆ የቆየውን የሀገር ሉአላዊነት አናስደፍርም ሲሉም ነዋሪዎቹ በሰልፉ ገልጸዋል።

የዞኑ ነዋሪዎች “የለውጥ ጉዟችን በውስጥና በውጪ ጠላቶቻችን አይደናቀፍም” በሚል ሰልፉን እያካሄዱ መሆናቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በሰላማዊ ሰልፉ “ሕወሓት የኢትዮጵያውያን ሁሉ ጠላት ነው፣ የሸብር ቡድኑን ማስወገድ የኢትዮጵያን ህዝብ ህልውና ማረጋገጥ ነው፣ የሸኔና የወያኔ የጭካኔ እርምጃዎችን አጥብቀን እናወግዛለን፣ የአሸባሪውን ሕወሓት ቀቢፀ-ተስፋ በትግላችን እንመክታለን፣ ለቀረበልን የክተት ጥሪ በህዝባዊ ቁጭትና ፅናት ተሰልፈናል፣ አካባቢዬን እጠብቃለሁ፤ ሀገሬን ለማዳን እዘምታለሁ እና በእኛ መስዋዕትነት ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ ትኖራለች” የሚሉ መፈክሮች በመደመጥ ላይ ይገኛሉ፡፡