ይህ ፈታኝ ጊዜ ጀግኖች የሚወለዱበት ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጥቅምት 27/2014 (ዋልታ) “የመጨረሻው ከባዱ ምጥ ልጁ የሚወለድበት ነው፤ ይህ ፈታኝ ጊዜም ጀግኖች የሚወለዱበት ነው” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።

የኢትዮጵያ ልጆች ከጫፍ እስከጫፍ ተነሥተዋል፤ ፈተናዎቹ አጠንክረውናል፤ ፈታኞቻችን ሌሎች መንገዶችን አሳይተውናል ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ጽፈዋል።

ፊታቸውን ካዞሩብን ወዳጆች እጥፍ የቁርጥ ቀን ወዳጆች አግኝተናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቅጠሎች መሰብሰብ ዋርካ አያደርጋቸውም፤ የዋርካዎች መሰብሰብ ግን ደኑን የማይደፈር እያደረገው ነው ሲሉም አክለዋል።

የሚከፈል መሥዋዕትነት አለ፤ ያ መሥዋዕትነት ግን ኢትዮጵያን ዋጅቶ በዐለት ላይ ይተክላታል ብለዋል።