ኢትዮጵያዊያን በሀሰተኛ መረጃ ስርጭት ዘመቻ የከፈቱ መገናኛ ብዙኃንን እየተቃወሙ ነው

ጥቅምት 28/2014 (ዋልታ) በመስቀል አደባባይ የተቃውሞ ድምፃቸውን ለማሰማት የተሰባሰቡ በሺሕዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በሀሰተኛ መረጃ ስርጭት አገር የማፍረስ ዘመቻ የከፈቱ ዓለም ዐቀፍ መገናኛ ብዙኃንን እየተቃወሙ ነው፡፡

ሰልፈኞቹ ከአሸባሪዎቹ ሕወሓትና አጋሮቹ ጋር በመወገን ከፍተኛ የስም ማጥፋትና አገር የማሸበር ሴራ ላይ የተጠመዱ የውጭ አገራት መገናኛ ብዙኃን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና ኢትዮጵያ በፕሮፖጋንዳ የምትፈርስ የእምቧይ ካብ አለመሆኗን እያረጋገጡ ይገኛሉ፡፡

እንደሮይተርስ ያሉ መገናኛ ብዙኃን ኢትዮጵያን በኃይል እናፈርሳለን ብለው ሕዝባዊ መሰረት የሌላቸው ቡድኖችና ግለሰቦች ሲሰበሰቡ በቀጥታ ስርጭት ሽፋን መስጠታቸው ይታወሳል፡፡

እንደሲኤንኤን፣ ቢቢሲ፣ ዘ ቴሌግራፍ፣ ዘ ኒውዮርክ ታምስና ሌሎችም የሽብር ቡድኑ ደጋፊዎች ደግሞ መሬት ላይ የሌለን ነገር ሲዘግቡ ታይተዋል፡፡

ይህን ዓይን ያወጣ ቅጥፈትና ሴራ ከኢትዮጵያዊያን ባሻገር በርከት ያሉ የውጭ አገራት ጋዜጠኞችና የእውነት ተሟጋቾች እያጋለጡት ይገኛሉ፡፡