ሲጂቲኤን መላ ኢትዮጵያዊያን የአገራቸውን ሉኣላዊነት ለማስጠበቅ ከመንግሥት ጎን ቆመዋል አለ

ጥቅምት 28/2014 (ዋልታ) መላ ኢትዮጵያዊያን የሕወሓት ሽብር ቡድንን እስከ ወዲያኛው ለማጥፋት እና የአገራቸውን ሉኣላዊነት ለማስጠበቅ ከመንግሥት ጎን መሆናቸውን እያሳዩ ነው ሲል የቻይናው ሲጂቲኤን ዘገበ።
በአዲስ አበባ ከተማ በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን የሕወሓት የሽብር ቡድንንና አጋሮቹን በማውገዝ መንግሥት ያቀረበውን አገራዊ ጥሪ መቀበላቸውን በድጋፍ ሰልፍ ገልጸዋል ብሏል፡፡
በመዲናዋ በርካታ ወጣቶች መከላከያ ሰራዊትን መቀላቀላቸውን የመገናኛ ብዙኃኑ ዘግቧል።
በተመሳሳይ በሌሎች ከተሞችም ሕዝቡ መከላከያን በመቀለላቀል እና አገሩን ከትግራይ ወራሪ ኃይል ለመጠበቅ እየዘመተ ያለበትን መረጃም ሲጂቲኤን ለዓለም አጋርቷል።