በህልውናችን ላይ የተደቀነብንን የመጥፋት አደጋ በዘላቂነት ለመቀልበስ ለፍጻሜው ትግል ከያለንበት እንነሳ – አቶ ግዛቸው ሙሉነህ

ጥቅምት 28/2014 (ዋልታ) የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ግዛቸው ሙሉነህ ባስተላለፉት መልዕክት “በአሸባሪውና ወራሪው ሕወሓት አማካይነት በህልውናችን ላይ የተደቀነብንን የመጥፋት አደጋ በዘላቂነት ለመቀልበስ የምንችለው በአሸናፊነት እንዲደመደም ማድረግ ስንችል ብቻ መሆኑን አምነን ለፍጻሜው ትግል ከያለንበት እንነሳ” ብለዋል።
ኃላፊው ያስተላለፉት ሙሉ መልዕክት ቀጥሎ ቀርቧል:-
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል አማራ እና አማራነትን ከምድረ ኢትዮጵያ ለማጥፋት የጠነሰሰውን ሥውር ሴራ አደገኛነት ለማረጋገጥ በአሁኑ ወቅት በወረራቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ውስጥ እየፈጸማቸው የሚገኙትን የአውሬ ድርጊቶች ለአፍታ ያህል ማስታወስ በቂ ነው፡፡
ይህ የአውሬዎች ማኅበር መላው አማራን ለማጥፋት ካለው እኩይ ርዕይ የተነሳ የአማራ ማንነት ያላቸውን ሰብዓዊ ፍጡራንን ሁሉ የእድሜ እና የጾታ ልዩነቶች ሳይወስኑት በጅምላ ከመግደሉ ባሻገር አማራ የሆኑ ሰዎችን ብቻ ሳይሆን የአማራ የሆኑትን እንስሳትና እጽዋትን ሳይቀር የማውደም ተልእኮውን በገሃድ ሲፈጽም ይታያል፡፡
የአውሬው ማኅበርተኞች እግራቸው በወራሪነት በረገጠባቸው በሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ በሰሜን እና ደቡብ ወሎ እንዲሁም በዋግኸምራ ዞን ውስጥ በንጹሐን ሰዎች ላይ የፈጸሙት ግፍ የአውሬውን ማኅበርተኞችን በጦርነት ከማራገፍ በስተቀር ለፈጸሙብን በደል የሚመጥን የቅጣት ምት አይኖርም፡፡
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል መነኮሳትና ቀሳውስትን፣ መሻዒዎችና ዑለማዎችን፣ ጨቅላ ሕጻናትና አዛውንቶችን በጭካኔ የገደላቸው በአማራነታቸው እንጂ የፖለቲካ ተሳትፎ ስለነበራቸው አይደለም፡፡ ከዝርፊያቸው የተረፉትን ሁሉንም አይነት የመሰረተ ልማትና የልማት ተቋማትን ያወደመው የአማራ ሕዝብ ሀብት ስለሆኑ ብቻ ነው፡፡
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል በደረሰበት ሁሉ ገዳማትንና አድባራትን፣ መስጂዶችንና መድረሳዎችን፣ መጽሐፍ ቅዱስና ቁርዓን፣ ነዋየ ቅዱሳትና ጽላትን በእሳት ያነደደበት ምክንያት የአማራ ሕዝብ ስጋና ነፍሱን ለማነጽ የሚችልበትን መንፈሳዊም ሆነ ቁሳዊ ሀብቱን ለማሳጣት አውሪያዊ ተልእኮ ስላነገቡ ነው፡፡
በሴቶችና በእናቶች ላይ የፈጸሙት ነውረኛ የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች ከተራ የጾታ ጥቃትነት የተለየ ዓላማ ያለውና በአማራ ቤተሰቦችና በአማራነት ሥነ ልቦና ላይ የማይጠገን ስብራትን ለማድረስ ካላቸው ጥልቅ ጥላቻ የተነሳ ነው፡፡
ታዲያ በዚህ መጠን በአማራ እና አማራነት ላይ ግልጽ ጠላት ሆኖ ከደጃችን የተጋረጠውን የአውሬ ማኅበርተኞች ማዕበል በተቀናጀ ክንዳችን ከመቅበር የተሻለ ምን ምርጫ አለን?
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል አማካይነት በህልውናችን ላይ የተደቀነብንን የመጥፋት አደጋ በዘላቂነት ለመቀልበስ የምንችለው በእሱ ለኳሽነት የተጀመረው ጦርነትን በእኛ አሸናፊነት እንዲደመደም ማድረግ ስንችል ብቻ መሆኑን አምነን ለፍጻሜው ትግል ከያለንበት እንነሳ!
በዚህ ወቅት ጠላት አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ኃይል ከመፋለም በተቃርኖ የሚቆሙበትን መሬት መረዳት ያልቻሉ ግለሰቦችና ቡድኖች እንዲጠነቀቁ እንመክራለን። ወይ ተገደን የገባንበትን የህልውና ትግል አምነው ይቀላቀሉ ወይም ጠላትነታቸውን በይፋ ገልፀው ከጠላት ጋር ይሰለፉ። ሁለት ቦታ መቆም በፍፁም አይቻልም።
ክተት፣ ዝመት፣ መክት፣ አንክት!
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦