የደቡብ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ እየተወያዩ ነው

በደቡብ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

ጥቅምት 29/2014 (ዋልታ) በደቡብ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ እየተወያዩ ሲሆን በምክክር መድረኩ መቋጫ የጋራ የአቋም መግለጫ ያወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በምክክር መድረኩ ከአሸባሪው ሕወሓት ጋር ያበሩ የውጭ ታሪካዊ ጠላቶች የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማዳከም ዐብይ አጀንዳ በመቅረጽ እየሰሩ መሆናቸው ተገልጿል።

ኢትዮጵያውያን አንድ እንዳይሆኑ ከፋፋይ ስልቶችን በመጠቀም የውስጥ ፍላጎታቸውን ለማሟላት በሙሉ አቅማቸው እየሰሩ መሆናቸውም ተጠቁሟል።

በአሁኑ ሰዓት መላውን የአገሪቱን ህዝብ ያሳተፈ የኅልውና ዘመቻውን የማጠናከር ስራ እየተሰራ መሆኑም ተብራርቷል።

የሽብር ቡድኑ በሁሉም አካባቢዎች ሰርጎ ገቦችን በማስገባት ሀገር ለማተራመስ እየጣረ መሆኑም በምክክር መድረኩ ተወስቷል።

ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ እንዳመላከተው በመላው አገሪቱ የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አተገባበር ውጤታማ እንዲሆን በጋራ መስራት እንደሚገባም ተጠቁሟል።