ኢትዮጵያ የጥበብና የመቻል አቅም ባለቤት ነች – ቻይና

ጥቅምት 30/2014 (ዋልታ) ቻይና፤ ኢትዮጵያ የጥበብና የመቻል አቅም ባለቤት ነች ስትል ገለፀች፡፡

ኢትዮጵያዊያን በዚህ አስቸጋሪ ወቅት በአንድነት ቆመው ወደ ቀደመ ሰላምና መረጋጋታቸው እንደሚመለሱም እምነት እንዳላት በተባበሩት መንግሥታት የቻይና አምባሳር ዣንግ ጁን ትናንት ለተሰበሰበው የፀታው ምክር ቤት አስረድተዋል፡፡