መንግሥት አሸባሪን ለማዳን የሚደረግን የውጭ ጣልቃ ገብነት አስጠነቀቀ

ኅዳር 8/2014 (ዋልታ) የአሸባሪውን ሕወሓትና ጀሌዎቹን ዓላማ ለማሳካት እየተደረገ ያለው ያልተገባ የውጭ ጣልቃ ገብነት ሊቆም እንደሚገባው መንግሥት አሳሰበ፡፡

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታው ከበደ ደሲሳ  በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸው ከጣልቃ ገብነት አንጻር የምዕራባዊያን መገናኛ ብዙኃን የኢትዮጵያን እውነታ ያላገናዘበና ከእውነት የራቀ መረጃዎችን በማሰራጨት ዓለም ዐቀፉን ማኅበረሰብ እያወዛገቡ እንደሆነ አስታውሰዋል፡፡

በሀሰተኛ የመረጃ ስርጭት ዘመቻውም አንዳንድ እውነት የመሰላቸው አገራት ዜጎቻቸውን ለማስወጣት እስከመሞከር ደርሰዋል ብለዋል፡፡

በአስቸኳይ አዋጁ ምክንያት ዜጎች በማንነታቸው እየተለዩ ይታሰራሉ በሚልም ሀሰተኛ መረጃ እያሰራጩ ነበር በማለትም ከእውነት የራቀ መሆኑን አስምረዋል፡፡

መንግሥት በተለያዩ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊን ጣልቃ ገብነትን የሚያወግዝ ሰልፎችን እያደረጉ መሆኑን ጠቅሶም አመስግኗል፡፡