ከሳዑዲ አረቢያ 472 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመለሱ

ከሳዑዲ አረቢያ ተመላሽ ዜጎች

ኅዳር 8/2014 (ዋልታ) በሳውዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ አገራቸው ለመመለስ እየተደረገ ባለው ጥረት 146 ህጻናትን ጨምሮ 472 ዜጎች ከጂዳ ሳዑዲ አረቢያ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል ተወካይ ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል እንደተደረገላቸው ከሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።