ሴቶች ሠላምን በመገንባት ረገድ ያላቸው ሚና ከፍተኛ ነው – ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ


ኅዳር 9/ 2014 (ዋልታ)
ሴቶች ተጠቂዎች ብቻ ሳይሆኑ በመፍትሄ አመንጪነት ግጭት እንዳይከሰት አስቀድሞ በመከላከል፣ በሰላማዊ ድርድር፣ በሽምግልና እና ከታችኛው እርከን ጀምሮ ሠላምን በመገንባት ያላቸው ሚና ከፍተኛ ነው ሲሉ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ፡፡

ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ይህን ያሉት የአፍሪካ ሴቶች መሪዎች ኔትወርክ በበይነ መረብ ባካሄደው 3ኛው የአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን የሴቶች መሪዎች ፎረም ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ላይ ነው፡፡