ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለሰራዊቱ የ150 ሚሊዮን የአይነትና የብር ድጋፍ አደረገ

ኅዳር 11/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለመከላከያ ሰራዊት የ150 ሚሊዮን የአይነትና የብር ድጋፍ አደረገ።

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለመከላከያ ሰራዊት በሶስቱ ዙር ባደረገው ድጋፍ ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል።

ክፍለ ከተማው ለሰላም ዘብ የሆኑ ከ13ሺሕ በላይ ህዝባዊ ኃይልንም አስመርቋል።

በምረቃ ስነ ሥርዓቱ የተገኙት የአዲስ አበባ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ቡዜ አልቃድር ይሄንን የኅልውና ጦርነት አሸንፈን ኢትዮጵያ አድጋ እና በልፅጋ፣ ታፍራ እና ተከብራ ትቀጥላለች ብለዋል፡፡

ተመራቂዎቹ “ከጥንትም በሀገር ሰላም አንድነት የሚደራደሩ ልጆች የሌሏት ኢትዮጵያ ዛሬም በእኛ ትከበራለች” ሲሉ ገልፀዋል።

በሀኒ አበበ