እንደ አድዋ ልጆች ኢትዮጵያን በጽናት ወደፊት እናሻግራለን – ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ኅዳር 12/2014 (ዋልታ) “በኢትዮጵያ እና በውጭ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ፣ እውነትን ለዓለም ለመግለጥ እያደረጋችሁ ያላችሁት ተጋድሎ እጅግ የሚደነቅ ነው” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው “ይህ ጥንታዊ ሕዝብ ከሩቅ እና ከቅርብ ኃይሎች የተጋረጠበትን የህልውና ስጋት አንድ ሆነን ማሸነፍ እንችላለን” ብለዋል።
እንደ አድዋ ልጆች ኢትዮጵያን በጽናት ወደፊት እናሻግራለን ሲሉም አስገንዝበዋል።