አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ አገሩን ለመታደግ ወደ ግንባር ለመዝመት መወሰኑን አስታወቀ

አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ

ኅዳር 14/2014 (ዋልታ) አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ ተከትሎ አገሩን ለመታደግ ወደ ግንባር ለመዝመት መወሰኑን አስታውቋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሳኔ ትክክል ነው ያለው አትሌት ፈይሳ በዚህ ሰዓት በአገራችን ላይ የተቃጣውን ችግር ልክ አባቶቻችን በዓድዋ እንዳደረጉት እኔም በግንባር ሄጄ የሚጠበቅብኝን እወጣለው ብሏል።

አትሌ ፈይሳ ሌሊሳ ፈጥነው የጠቅላይ ሚነስትሩን ጥሪ ከተቀበሉ መካከል አንዱ ነው።