መንግሥት ዲያስፖራዎች በገንዘብ ድጋፍ እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረበ

ኅዳር 14/2014 (ዋልታ) መንግሥት ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች በገንዘብ ድጋፍ በመሳተፍ ለወገናቸውና አገራቸው እንዲደርሱ ጥሪ አቀረበ።
የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ባቀረበው ጥሪ ዲያስፖራዎች ውጭ ያለው አካላቸው እንጂ ልባቸው ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን እያደረጉ ባሉት ሁለንተናዊ ድጋፍ አረጋግጠዋል ብሏል።
በመሆኑም ከሳምንት በፊት በተጀመረውና ከታሰበው ቀድሞ ከ1 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ በተሰበሰበበት የአይዞን ኢትዮጵያ (https://t.co/raA6oJF0zo) የቀጥታ በይነመረብ ድጋፍ ማድረጊያ በኩል ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ ነው ጥሪ ያቀረበው።