ፈረንሳይ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ከ1 ሚሊዮን ዩሮ በላይ ድጋፍ አደረገች

ኅዳር 15/2014 (ዋልታ) ፈረንሳይ በኦሮሚያ ክልል በቦረና አካባቢ በድርቅ ለተጎዱ የኅብረተሰብ ክፍሎች 1 ሚሊዮን 76 ሺሕ 687 ዩሮ ድጋፍ አድርጋለች።

እርዳታው በድርቁ ሳቢያ ችግር ውስጥ የወደቁ ዜጎችን ለመታደግ እንደሚያግዝ በኢትዮጵያ ከፈረንሳይ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።