ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለአዲሱ ክልል የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተለላለፉ

ኅዳር 15/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ ሕገ መንግሥታዊ መብቱን ተጠቅሞ 11ኛ ክልል ለሆነው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተለላለፉ፡፡

ብዝኃነት የአንድነት አንዱ ምሰሶ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በቲውተር ገጻቸው ጽፈዋል፡፡

የ11ኛው ክልል መመስረትም የለውጡ ሂደቱ አንዱ ውጤት ነው ብለዋል፡፡

የፌደራል ስርዓት ዜጎች ራሳቸውን የሚያስተዳድሩበትና አገራቸውን የሚገነቡበት የአስተዳደር ስልት ነው ሲሉም አክለዋል፡፡ ይህንንም በተግባር እያሳየን ነው ሲሉ ጽፈዋል፡፡